የሳኅል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የጋራ ወታደራዊ ኃይሉን በአምስት እጥፍ ሊያሳድግ ነው
15:58 28.07.2026 (የተሻሻለ: 16:04 28.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሳኅል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የጋራ ወታደራዊ ኃይሉን በአምስት እጥፍ ሊያሳድግ ነው
ኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ በጋራ ያቋቋሙትን ወታደራዊ ኃይል በሚመጡት ዓመታት ውስጥ ከ5,000 ወደ 18,000 ወታደሮች ለማሳደግ ማቀዳቸውን የኒጀር ፕሬዚዳንት አብዱራሃማኔ ቲያኒ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል።
የኦፕሬሽን እንቅስቃሴ፦
እ.ኤ.አ. በ2025 የተቋቋመውና መቀመጫውን ኒያሜ ያደረገው ይህ የጋራ ኃይል፣ እስካሁን በምስጢር የተያዙ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን ማካሄዱ ተገልጿል።
የተጠናከረ የውህደት ጥረት፦
የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን ከወታደራዊ ትብብሩ በተጨማሪ የጋራ ፓስፖርት፣ የቴሌቪዥን ጣቢያ፣ ባንክ እና አየር መንገድ በመክፈት አካባቢያዊ ውህደቱን የበለጠ ለማጠናከር እየሠራ ይገኛል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X