ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው
ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.07.2026
ሰብስክራይብ

ደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኮሎምቢያ በኢትዮጵያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ያሉ ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው

የኢምባሲዎቹ መዘጋት የኮሎምቢያ ተመራጩ ፕሬዚዳንት አቤላርዶ ደ ላ ኤስፕሪዬላ የሀገራቸውን የዲፕሎማሲ መዋቅር በጥልቀት ለማሻሻል የሚያደርጉት ጥረት አካል መሆኑ ተዘግቧል።

የዲፕሎማሲ ወጪን ለመቀነስ እና የዓለም አቀፍ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማስተካከል በአፍሪካ የሚገኙ 4 ኤምባሲዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ኤምባሲዎች እንደሚዘጉ ተገልጿል።

ከአንድ ዓመት በፊት፣ የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዝዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቴዎስ በተገኙበት፤ ኮሎምቢያ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን በይፋ ደግማ መክፈቷ ይታወሳል፡፡

ኮሎምቢያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ኤምባሲ የከፈተችው እ.አ.አ. በ1967 ሲሆን፣ በ1974 ተዘግቶ ነበር። ሁለቱ ሀገራት እ.አ.አ. ከ1949 ጀምሮ የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0