በ2018 በጀት ዓመት 1.518 ትሪሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል - ገቢዎች ሚኒስቴር
12:15 28.07.2026 (የተሻሻለ: 12:24 28.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ2018 በጀት ዓመት 1.518 ትሪሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል - ገቢዎች ሚኒስቴር
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባካሄዱት የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ፣ የተሻሻለውን ዓመታዊ የገቢ ዕቅድ (1.50 ትሪሊዮን ብር) ማሳካታቸውን አስታውቀዋል።
ከሀገር ውስጥ ታክስ 780.4 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 738.2 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል።
አፈጻጸሙ ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ618.39 ቢሊዮን ብር (የ68.69%) ዕድገት አሳይቷል።
በቀጣይ በጀት ዓመት የተያዘውን 2 ትሪሊዮን 83 ቢሊዮን ብር የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ደንበኛ ተኮር አገልግሎት፣ የታክስ መሠረትን ማስፋት፣ የታክስ ሕግ ተገዥነትን ማሳደግ እና የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X