የአፍሪካ ቀጣይ የኃይል ሚዛን በባሕር ላይ የተመሠረተ ነው - ባለሙያ
09:03 28.07.2026 (የተሻሻለ: 09:04 28.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ቀጣይ የኃይል ሚዛን በባሕር ላይ የተመሠረተ ነው - ባለሙያ
የአፍሪካ የባሕር ላይ ኃይልና ሉዓላዊነት የጦር መርከቦችን ከመግዛት ያለፈ ጥልቅ ስትራቴጂን እንደሚጠይቅ በደቡብ አፍሪካ የስቴለንቦሽ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጂክ ጥናት ተመራማሪዋ ዶ/ር ጆአን ስዋርት ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።
ተመራማሪው በገለፃቸው፣ "የባሕር ሉዓላዊነት የውኃ ክልልን ከመጠበቅ ባሻገር ንግድን፣ የተፈጥሮ ሀብትንና መሠረተ ልማትን የመጠበቅ እንዲሁም ሕግን የማስከበር አቅም ነው" ብለዋል።
ባለብዙ-ዋልታ በሆነው የዛሬው ዓለም፣ አፍሪካ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር የሚኖራት ግንኙነት ከጥገኝነት ይልቅ በራስ አቅም እና በስትራቴጂካዊ አማራጮች ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
በዚህ ረገድ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት፣ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ፣ የሀገር ውስጥ ፈጠራ እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚደረግ የጠበቀ ትብብር ለሰማያዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆናቸውን ዶ/ር ጆአን ስዋርት አመላክተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X