በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ሩሲያ ወደ አፍሪካ የምትልካቸው የግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ በ40% አደገ - አግሮኤክስፖርት
08:25 28.07.2026 (የተሻሻለ: 08:34 28.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ሩሲያ ወደ አፍሪካ የምትልካቸው የግብርና ምርቶች የወጪ ንግድ በ40% አደገ - አግሮኤክስፖርት
ሩሲያ ወደ አኅጉሪቱ በግምት 2.9 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ከ11 ሚሊዮን ቶን በላይ የግብርና ምርቶችን ማቅረቧን የሩሲያ የግብርና ኤክስፖርት ልማት ማዕከል (አግሮኤክስፖርት) አስታውቋል።
በመጠን ከፍተኛ የሆኑ የወጪ ንግድ ምርቶች፦
ስንዴ፦ ~10.2 ሚሊዮን ቶን
ገብስ፦ ~234,000 ቶን
የአኩሪአተር ዘይት፦ ከ158,000 ቶን በላይ
የሱፍ ዘር ተረፈ-ምርት እና ዱቄት መኖ፦ ከ95,000 ቶን በላይ
የስኳር ቢት (ባቄላ) ተረፈ-ምርት ፦ ከ64,000 ቶን በላይ
ዋና ዋና ሸማቾች፦
ግብፅ 4.9 ሚሊዮን ቶን በመግዛት እና ከአጠቃላይ መጠኑ 44% ድርሻ በመያዝ በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡
ሱዳን የ11% ድርሻ በመያዝ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
ኬንያ የ10% ድርሻ በመያዝ ሦስተኛዋ ግዙፍ ገዢ ነች።
በጠቅላላው ሩሲያ በ2026 የግብርና ምርቶችን ከ40 በላይ ለሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መላኳን አግሮኤክስፖርት አመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X