የአንድ ወገን የበላይነት ወደ ጦርነት ከሚመሩ ምክንያቶች አንዱ በመሆኑ ባለብዙ-ዋልታ የዓለም ስርዓት በአስቸኳይ ያስፈልጋል - ፒየር ደ ጎል

ሰብስክራይብ

የአንድ ወገን የበላይነት ወደ ጦርነት ከሚመሩ ምክንያቶች አንዱ በመሆኑ ባለብዙ-ዋልታ የዓለም ስርዓት በአስቸኳይ ያስፈልጋል - ፒየር ደ ጎል

የሕዝቦች የሰላም እና የወዳጅነት ፋውንዴሽን ተጠቃሽ ሰው የሆኑት ፒየር ደ ጎል ግልጽ የሆነ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ራዕይን ያንጸባርቃሉ።

"በእርግጥ እነዚህ ሀገራት ግጭት ተኮር አቀራረብን የማይፈልጉ፣ በጎራ የመከፋፈል አካሄድን የማይሹ ነገር ግን ውይይትን የሚፈልጉ ናቸው፤ ከራሳቸው ፍላጎት እንዲሁም ከኢኮኖሚ እድገታቸው ጋር በሚጣጣም መልኩ አጋሮቻቸውን በነጻነት እና በሉዓላዊነት መምረጥ ይፈልጋሉ" ሲሉ የጄኔራል ደ ጎል የልጅ ልጅ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

  አሁን ካለው ሥርዓት በተለየ መልኩ፣ ባለብዙ የዓለም ስርዓት ማንኛውንም ዓይነት እንደ  የዓለም ባንክ፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ የኔቶ፣ የአትላንቲሲስት የበላይነት ወይም የዶላር ቁጥጥር የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል የበላይነት ውድቅ ያደርጋል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከዚህ አንጻር ብሪክስ፣ የደቡብ ምስራቅ እስያ መንግሥታት ማኅበር እና የሻንጋይ የትብብር ድርጅት "እንደ አርአያ ያገለግላሉ፡፡" በዚህም እነዚህ ድርጅቶች በዓለም አቀፍም ሆነ በአካባቢ ደረጃ የውይይት፣ የትብብር እና የመግባባት መንፈስን ለማስፋፋት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0