የ"ደስታ መሰል" በሽታ ክትባት በማምረት ችግሩን በራሷ አቅም መቆጣጠር የሚያስችል አቅም ገንብታለች - ግብርና ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

የ"ደስታ መሰል" በሽታ ክትባት በማምረት ችግሩን በራሷ አቅም መቆጣጠር የሚያስችል አቅም ገንብታለች - ግብርና ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የበጎችና የፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ተከስቶ የነበረ ቢሆንም ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤና እና የቬተርናሪ ማኅበረሰብ ጤና መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሲሳይ ጌታቸው የበጎችን እና ፍየሎችን ደስታ መሰል ከአፍሪካ ለማጥፋት ያለመ አኅጉራዊ የምክክር መድረክ ባደረጉት የመከፈቻ ንግግር ላይ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በእንስሳት ጤና እንስትቲውት አማካይነት ከበቂ በላይ የሆነ አስተማማማኝነቱ በአኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የተረጋገጠ የበጎችና የፍየሎች ደስታ መሳይ በሽታ ክትባት እያመረተች ነው ያሉት ዶ/ር ሲሳይ፤ ይህም ሃገሪቱ ችግሩን በራሷ አቅም እንድትቆጣጠር እንዳስቻላት ገልጸዋል።

ሆኖም ወረርሽኙ በዋነኝነት የሚከሰተው በንግድ ምክንያት በሚደረግ የቤት እንስሳት እንቅስቃሴ፣ በአርብቶ አደሮች በአገራት አዋሳኝ አካባቢዎች በሚደረግ ዝውውር አማካይነት የሚከሰት በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመቆጣጠር ያላሰለሰ የቅኝት፣ የክትትል አና የቁጥጥር ሥራ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

ዶ/ር ሲሳይ፣ ድንበር ተሻጋሪ የአገራት የጋራ ጥረት በሽታውን ለማጥፋት ወሳኝ መሆኑን ማሳሰባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

  ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0