ዚምባብዌ የገጠር ግብርናን ለማዘመን 35 ሺህ ትራክተሮችን ልታከፋፍል ነው - ዘገባ

ሰብስክራይብ

ዚምባብዌ የገጠር ግብርናን ለማዘመን 35 ሺህ ትራክተሮችን ልታከፋፍል ነው - ዘገባ

በሁለተኛው ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ስር ቀደም ሲል ይፋ የተደረጉ ዕቅዶችን በመከተል፣ መንግሥት የምርታማነትን አቅም ለማሳደግ እና ሀገራዊ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም መንደሮች የትራክተር አቅርቦት እያሰራጨ እንደሚገኝ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የዚሁ ጥረት አካል የሆነውን እና ባህላዊውን በዶማና በሞፈር-ቀንበር የማረስ ዘዴ ወደ ገበያ ተኮር የመንደር የንግድ ክፍሎች* ለማሸጋገር ያለመውን የሜካናይዜሽን ፕሮግራም ፕሬዚዳንት ምናንጋግዋ በይፋ ያስጀምራሉ።

እስካሁን ስላለው የስርጭት ሂደት የመገናኛ ብዙኃን የሜካናይዜሽን፣ ውሃ እና የገጠር ማሰፈሪያ ሚኒስትሩን አንክሺየስ ማሱካን ጠቅሰው እንደዘገቡት፦

በሀገሪቱ የሚገኘው የትራክተር ቁጥር ከእጥፍ በላይ ያደገ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2017 ከነበረበት 7,500 አሁን ላይ ወደ 17,800 አድጓል።

ተጨማሪ 5,000 ትራክተሮች በቅርቡ ተደራሽ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

መንግሥት መሣሪያዎቹን ለማስገባትና ለማከፋፈል ከ11 አከፋፋዮች ጋር እየሰራ ይገኛል።

* የመንደር የንግድ ክፍሎች የመንደሩ ነዋሪዎች ምርቶችን በጋራ እንዲያመርቱና ለገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችሉ ሲሆን፣ ለታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል የሥራ ዕድል በመፍጠር የቤተሰብ ገቢን ያሳድጋሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0