ዩክሬናውያን በማሊ ጥቃት የሚሠነዝሩ ቅጥረኞችን የሚያሠለጥኑት በኮትዲቯር ጫካዎች ውስጥ ነው - የኒጀር ፕሬዚዳንት
08:30 27.07.2026 (የተሻሻለ: 08:34 27.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩክሬናውያን በማሊ ጥቃት የሚሠነዝሩ ቅጥረኞችን የሚያሠለጥኑት በኮትዲቯር ጫካዎች ውስጥ ነው - የኒጀር ፕሬዚዳንት
ዩክሬናውያን በሚያዝያ ወር ማሊ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጀርባ የነበሩ ቅጥረኞችን በማሠልጠን መሳተፋቸውን አብዱራህማን ቲያኒ ለሚዲያ ተናግረዋል።
ከዩክሬን አጎራባች ሀገር ባገኙት ቪዛ ተጠቅመው ኮትዲቯር ውስጥ በሚገኝ ጫካ ማረፋቸውንም ገልጸዋል።
ቲያኒ በተጨማሪም እ.አ.አ ሚያዝያ 25 ከአል-ቃይዳ* ጋር ግንኙነት ባለው አሸባሪ ቡድን ባደረሰው ጥቃት እና የማሊ መከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ ተሽከርካሪያቸው በአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ በተገደሉበት ክስተት ሦስት አጎራባች የአፍሪካ ሀገራት የነበራቸውን "ተባባሪነት" አውግዘዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተመሳሳይ የቀድሞ ቅኝ ገዥ ኃይሎች "አሸባሪ ቡድኖችን ብቻ ሳይሆን የዩክሬን ተዋጊዎችንም ጭምር" ለሚጠቀሙ የሳኅል እስላማዊ ቡድኖች የሚያደርጉትን ድጋፍ ሐምሌ ወር አጋማሽ አውግዘው ነበር።
*ሩሲያ ውስጥ የታገደ አሸባሪ ድርጅት
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X