ሩሲያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ባሕር ኃይል ሥርዓት ክፍለ ጦር አቋቋመች

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ባሕር ኃይል ሥርዓት ክፍለ ጦር አቋቋመች
ሩሲያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ባሕር ኃይል ሥርዓት ክፍለ ጦር አቋቋመች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.07.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ባሕር ኃይል ሥርዓት ክፍለ ጦር አቋቋመች

​"የሰሜን ባሕር ኃይል ሰው አልባ የውሃ ላይ እና የውሃ ውስጥ መርከቦችን የታጠቀ ክፍለ ጦር ቀድሞውንም ያለው ሲሆን በቀጣይ ዓመት በፓስፊክ የባሕር ኃይል ተመሳሳይ ክፍል ለማቋቋም ታቅዷል" ሲሉ የሩሲያ የባሕር ኃይል ዋና አዛዥ አሌክሳንደር ሞይሴየቭ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።

​ቁልፍ ነጥቦች፦

​ ሩሲያ 9,000 ቶን የሚመዝን አዲስ የውቅያኖስ አቋራጭ የ 'ፍራይጌት' ምድብ የውሃ መርከብ ትገነባለች።

​ 'አድሚራል ናኪሞቭ' የተሰኘችው ከባድ እና በኒውክሌር ኃይል የምትንቀሳቀሰው ሚሳኤል ታጣቂ የጦር መርከብ ከእድሳት በኋላ የባሕር ሙከራዋን እያጠናቀቀች ሲሆን በዚህ ዓመት መገባደጃ የሩሲያን የባሕር ኃይል ትቀላቀላለች ተብሎ ይጠበቃል።

​ ሩሲያ የባሕር ሰርጓጅ መርከቦችን እንድትለይ የተነደፈችውን የመጀመሪያዋን ሰው አልባ ባለ 500 ቶን መርከብ እየገነባች ነው።

​ 'ፖሳይዶን' ለተሰኘው ሰው አልባ የውሃ ውስጥ ተሽከርካሪ የሚያገለግል ተሸካሚ መርከብ ቀድሞውኑ በሩሲያ የባሕር ኃይል ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0