ብርቅዬ የኑቢያን ቀጭኔዎች ወደ ኡጋንዳ ተዛወሩ

ሰብስክራይብ

ብርቅዬ የኑቢያን ቀጭኔዎች ወደ ኡጋንዳ ተዛወሩ

​ ባለሥልጣናት የሀገሪቱን 40% የነዳጅ ክምችት በያዘው ክልል ውስጥ ከፍተኛ የዱር እንስሳት ጥግግት የሚያስከትለውን አደጋ ለመቀነስ፤ ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸውን12 የኑቢያን ቀጭኔዎችን ከሙርቺሰን ፎልስ ፓርክ 106 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው የአጃይ መጠባበቂያ ስፍራ አዛውረዋል።

​ማደንዘዣ ተሰጥቷቸው እና ዓይኖቻቸው ታስረው በመንገዳቸው የዛፍ ቅርንጫፎች አየበሉ በልዩ ሁኔታ በተዘጋጁ የጭነት መኪናዎች ከተጓጓዙ በኋላ ስፍራው በአዲሱ መኖሪያቸው ተለቀዋል።

​ℹ የአጃይ የጥበቃ ስፍራ በ1980ዎቹ በሕገ-ወጥ አደን ምክንያት የዱር እንስሳቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጠፍተው ነበር። ዛሬ ላይ ግን ነጭ አውራሪሶች፣ ጎሾች እና የሜዳ አህዮች ወደ ስፍራው ዳግም እየተዋወቁ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0