የአሜሪካ ጦር ባለፉት ሁለት ሳምንታት የ20.6 ቢሊዮን ዶላር ውድመት ማስተናገዱ ተዘገበ

ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ጦር ባለፉት ሁለት ሳምንታት የ20.6 ቢሊዮን ዶላር ውድመት ማስተናገዱ ተዘገበ

በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር መሣሪያ እና መሠረተ ልማቶች በቅርቡ በከፍተኛው እንደወደሙ፤ ከእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ተወካይ የተገኘን መረጃ ከፔንታጎን የበጀት እና የምትክ ወጪ ግምቶች ጋር በማያያዝ የተደረገ ትንተና ማሳየቱን አንድ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

የውድመቱ ዝርዝር፦

የአየር መከላከያ እና ራዳሮች፦ በግምት 7.5 ቢሊዮን ዶላር፣
ሎጅስቲክ፣ መጋዘኖች እና መሠረተ ልማት፦ በግምት 6.8 ቢሊዮን ዶላር፣
አውሮፕላኖች፣ ድሮኖች እና ሄሊኮፕተሮች፦ በግምት 3.5 ቢሊዮን ዶላር፣
የዕዝ እና የመገናኛ ማዕከላት፦ በግምት 2.8 ቢሊዮን ዶላር።

የጦር መሣሪያ ኪሣራው፤ የፓትሪዮት የአየር መከላከያ ስርዓቶችን፣ የራዳር ተከላዎችን፣ የኤፍ-15 የዉጊያ ጄቶችን፣ የአየር ላይ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖችን፣ ድሮኖችን፣ የጥይት መጋዘኖችን እና በርካታ የዕዝ እና የሎጅስቲክ ማዕከላትን ያካትታል።

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ በአሜሪካ የጦር መሠረተ ልማት ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ያሳያል የተባለ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ቪዲዮ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0