የሳኅል ሀገራት ጥምረት ከአውሮፓ ጋር ቢፋጠጥም አንድነቱንና ተቋሞቹን እያጠናከረ ነው - የኒጀር ፕሬዚዳንት
16:49 26.07.2026 (የተሻሻለ: 16:54 26.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሳኅል ሀገራት ጥምረት ከአውሮፓ ጋር ቢፋጠጥም አንድነቱንና ተቋሞቹን እያጠናከረ ነው - የኒጀር ፕሬዚዳንት
የጥምረቱ አባል ሀገራት የአውሮፓ ኃይሎችን ተቃውሞ ተቋቁመው በመከላከያ፣ በዲፕሎማሲ እና በልማት ዘርፎች ይህን ነው የሚባል እርምጃዎችን እንደወሰዱ አብዱራሃማኔ ቲያኒ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
"በኢማኑኤል ማክሮን ከሚመራው የአውሮፓ ኃይል ጋር ጦርነት ላይ ነን" ሲሉ ፕሬዚዳንቱ የጥምረቱን ጥንካሬ እና ስኬቶች አስረድተዋል።
እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ የተመዘገቡት ዋና ዋና ስኬቶች የሚከተሉት ናቸው፦
▪ መከላከያ፦ መቀመጫውን ኒያሜ ያደረገውና ከኒጀር፣ ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ የተውጣጣው የ5,000 ወታደሮች የተቀናጀ የጥምረቱ ኃይል፤ የጋራ ወታደራዊ እርምጃዎችን ማካሄድ የጀመረ ሲሆን በቀጣይ የሠራዊቱን ቁጥር ወደ 18 ሺህ ለማሳደግ አቅዷል።
▪ ልማት፦ የኢንቨስትመንት እና ልማት ኮንፌዴሬሽን ባንክ መቋቋሙ ሌላው ትልቅ ስኬት ነው።
▪ ዲፕሎማሲ፦ የሳኅል ሀገራት ጥምረት "በአንድ ድምፅ መናገር" በመጀመሩ በአንድ ወቅት በኮንፌዴሬሽኑ ይሳለቁ የነበሩ አካላት አሁን አምነው እንዲቀበሉት አስገድዷቸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X