የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን የአፍሪካ ፓትርያርክ በታንዛኒያ የመጀመሪያውን ቤተ-ክርስቲያን ባረኩ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን የአፍሪካ ፓትርያርክ በታንዛኒያ የመጀመሪያውን ቤተ-ክርስቲያን ባረኩ

የአፍሪካ ፓትርያርክ ጳጳስ ኮንስታንቲን፤ በታንዛኒያ ለቅዱስ ኒቆላዎስ መታሰቢያነት ለተገነባው ቤተ-ክርስቲያን አነስተኛ የባርኮት ሥነ-ሥርዓት አከናውነው ቅዳሴውንም እንደመሩ፤ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን የአፍሪካ ፓትርያርክ አስታውቋል።

በኪማምባ መንደር በፓትርያርኩ የለጋሾች ድጋፍ የተገነባው ይህ ቤተ-ክርስቲያን ግንባታው ወደ መጠናቀቁ የተቃረበ ሲሆን ቀሪ የማጠናቀቂያ እና የአካባቢ ማስዋብ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

ጳጳስ ኮንስታንቲን ከመንፈሳዊ ትምህርታቸው በኋላ ለደብሩ የቅዱስ ኒቆላዎስን ሥዕለ አድኅኖ እና አረንጓዴ የቅዳሴ አልባሳትን እንዳበረከቱ እንዲሁም ለሁሉም ምዕመናን ሥዕለ አድኅኖ እና የአንገት መስቀሎችን እንዳደሉ ፓትርያርኩ ገልጿል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0