ከቻይና ጋር የሚደረገው የኤአይ ትብብር የኢትዮጵያን የሚቲዎሮሎጂ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች እያሳደገ ነው - ባለሥልጣን
14:28 26.07.2026 (የተሻሻለ: 14:34 26.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከቻይና ጋር የሚደረገው የኤአይ ትብብር የኢትዮጵያን የሚቲዎሮሎጂ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች እያሳደገ ነው - ባለሥልጣን
ከቻይና ሜቲዎሮሎጂ አስተዳደር እና ከሌሎች የቻይና አጋሮች ጋር የተፈጠረው የተጠናከረ አጋርነት ወደ ኢትዮጵያ ዘመናዊ የብሔራዊ የአየር ሁኔታ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች እንዲገቡ ማስቻሉን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ ለቻይና ሚዲያ ገልጸዋል።
የሁለቱ ሀገራት የሜቲዎሮሎጂ ተቋማት በቴክኒክ ትብብር፣ የአቅም ግንባታ፣ በአየር ጠባይ እና አየር ንብረት ትንበያ እንዲሁም አደጋን በመቀነስ ዙሪያ በቅርቡ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ ሁለቱ አካላት ትክክለኛ እና ጥራት ያለው የአየር ጠባይና አየር ንብረት መረጃ ለማመንጨት ኤአይ፣ የማሽን ሥልጠና እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ እያዋሉ ይገኛሉ።
"የምንኖረው በሰው ሠራሽ አስተውሎት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ዘመን ነው። የአየር ሁኔታ እና የአየር ንብረት መረጃን ለማሻሻል እና ይበልጥ ትክክለኛ ለማድረግ፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማሰማራት እና መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ቻይና ሠራሹን "ማዙ" የሚቲዎሮሎጂ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በማግኘት ቀዳሚ እንደሆነች እና ቴክኖሎጂውን የሚያስተዳድሩ ባለሙያዎች በቻይና ሳይንቲስቶች ከፍተኛ ሥልጠና እንደተሰጣቸውም ተጠቁሟል።
"የቀጥታ እንዲሁም የአጭር ጊዜ ትንበያዎችን ለማመንጨት የማዙን ስርዓትን ወደ ሥራ እያስገባን እንገኛለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X