የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ የአፍሪካን የኃይል ነፃነት ለማጠናከር ከግል ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ አገኘ

ሰብስክራይብ

የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ የአፍሪካን የኃይል ነፃነት ለማጠናከር ከግል ባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ አገኘ

​ የዳንጎቴ ግሩፕ በሌኪ፣ ናይጄሪያ የሚገኘውን የማጣሪያ ፋብሪካውን ማስፋፊያ ለመደገፍ፤ በአፍሪካ ትልቁ ይፋዊ የግል ኢንቨስትመንት ተብሎ በተገለጸው ሂደት 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሰብስቧል።

​ኩባንያው የአቅም ማስፋፊያ ፕሮግራሙን አጠናክሮ በሚገፋበት ወቅት ይህ ገንዘብ፤ የውስጥ የገንዘብ ፍሰቶችን እና የውጭ ፋይናንስን እንደሚደግፍ አሊኮ ዳንጎቴ ገልጸዋል።

​ ቀድሞውንም የአኅጉሪቱ ግዙፉ ማጣሪያ የሆነው ይህ ፋብሪካ፤ እ.ኤ.አ በ2028 የማምረት አቅሙን ከእጥፍ በላይ አሳድጎ በቀን ወደ 1.4 ሚሊዮን በርሜል ለማድረስ በወጠነው ዕቅድ፤ የህንዱን ጃምናጋር ፋብሪካ በመብለጥ በዓለም ግዙፉ ማጣሪያ ይሆናል።

​ይህ ማስፋፊያ አፍሪካ ከውጭ በሚገቡ የተጣሩ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ እና የአኅጉሪቱን የኃይል ደህንነት ለማጠናከር እንደሚያግዝ የዳንጎቴ ግሩፕ አስታውቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0