ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ በጭራሽ ለአንድ ወገን ያዘነበለ አይደለም - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ሰብስክራይብ

ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ በጭራሽ ለአንድ ወገን ያዘነበለ አይደለም - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

 

በምክክር መድረኩ የተለያዩ አካላት እኩልና ፍትሐዊ ውክልና እንዲኖር አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ እንደሆነ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አረጋግጠዋል።

በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተመጣጠነ ውክልና እንዲኖራቸው መደረጉን ገልጸዋል።

 

“ሀገራዊ ምክክሩ በውይይትና በመግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂና አዋጭ መፍትሔ ለማምጣት አስፈላጊ ሂደት ነው” ሲሉም አክለዋል።

 

በስምንት አጀንዳዎች ላይ የሚደረገውን ውይይት ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ መሸጋገሩን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0