የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲሸልስን የገበያ ምንጮች በማብዛት ጠቃሚ አጋር ሆኗል - የሲሸልስ ቱሪዝም ቦርድ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲሸልስን የገበያ ምንጮች በማብዛት ጠቃሚ አጋር ሆኗል - የሲሸልስ ቱሪዝም ቦርድ

አየር መንገዱ ሕዳር 22፣ 2019 ዓ.ም ጀምሮ በቀን ሁለቴ ወደ ሲሸልስ በሚያደርገው በረራ የደሰቲቱን ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ያሳድጋል ተብሏል።

በአዲስ አበባ እና በማሄ መካከል በቀን ሁለት ጊዜ የሚደረገው በረራ የመንገደኞች ወንበር አቅምን ከ1,000 በላይ በማሳደግ፤ ለሲሸልስ የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እና ሀገሪቷ ከአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ እና ሰሜን አሜሪካ ጋር ያላትን ትስስር ያጠናክራል ተብሎ ተጠብቋል።

"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሸልስ የገበያ ምንጮቿን ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚደግፍ ዋና አጋር ሆኗል።...ይህ ተጨማሪ አቅም ገበያ ከማብዛት ስትራቴጂያችን እና የሲሸልስን ተደራሽነት ከማሳደግ ዓላማችን ጋር ሙሉ በሙሉ የሚጣጣም ነው” ሲሉ የሲሸልስ ቱሪዝም ቦርድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቬስና ራኪች ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን አስረድተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0