ዚምቧቤ በ2030 የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን በሀገሪቱ ሙሉ በመሉ ተዳራሽ ለማድረግ ማቀዷን አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ዚምቧቤ በ2030 የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትን በሀገሪቱ ሙሉ በመሉ ተዳራሽ ለማድረግ ማቀዷን አስታወቀች

የዚምቧቤ መንግሥት በታዳሽ ኃይል ላይ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት በመጨመር እ.ኤ.አ በ2030 መቶ በመቶ የቤት ውስጥ ኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለማሳካት ማቀዱን በኃይልና ኢነርጂ ልማት ሚኒስቴር ቋሚ ሴክሬታሪ ግሎሪያ ማጎምቦ በመጀመሪያው የአፍሪካ የኢነርጂ ፎረም የዚምቧቤ ዝግጅት ላይ ገልጸዋል።

ሚኒስቴሩ ያጋሯቸው ዋና ዋና ግቦች እና አኃዞች፦

የኤሌክትሪክ መረብ ትስስር፦ በየዓመቱ በግምት 320 ሺህ ቤተሰቦች ከመስመር ጋር የሚገናኙ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2025 እስከ 2030 ባለው ጊዜ ደግሞ በየዓመቱ ተጨማሪ 200 ሺህ ቤተሰቦች ከዋና መስመር ውጭ የሆኑ የኃይል አማራጮችን ያገኛሉ።

የታዳሽ ኃይል አቅም፦ እ.ኤ.አ በ2024 ከነበረበት 1,282 ሜጋ ዋት ተነስቶ በ2030 ወደ 2 ሺህ 640 ሜጋ ዋት የሚያድግ ሲሆን ይህም ከታቀደው ጠቅላላ የኃይል አቅም እኩል ያህሉን ይሸፍናል።

የኃይል ስብጥር፦ የታዳሽ ኃይል ምንጮች ድርሻ (ታላላቅ የውኃ ኃይሎችን ሳይጨምር) በ2030 ከነበረበት 7.8 በመቶ ወደ 29 በመቶ ያድጋል።

በኔት-ሚተር የሚለካ የፀሐይ ኃይል፦ የሕዝቡንና የግል ዘርፉን ለማስፋፋት እ.ኤ.አ ከ2026 እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ 200 ሜጋ ዋት የፀሐይ ኃይል የማመንጨት አቅም ለማሳካት ታቅዷል።

ንጹህ የምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ፦ የቤተሰቦች የንጹህ ምግብ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ተደራሽነት በ2030 ከ38.6 በመቶ ወደ 70 በመቶ ከፍ ይላል።

በቀጣናው የኃይል ፍላጎት እየጨመረ የመጣው በኢንዱስትሪ ልማት፣ በማዕድን ልማት መስፋፋት እና በግብርና ዘመናዊነት ምክንያት እንደሆነ የዛምቤዚ ወንዝ ባለሥልጣን ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክሪስቶፈር ቺሴንሴ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0