የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ
17:10 25.07.2026 (የተሻሻለ: 17:14 25.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ
መኮንኖቹ በምክትል መቶ አለቃ ማዕረግ እና በዲግሪ የትምህርት መርኃ-ግብር የተመረቁ ናቸው። በወታደራዊ አካዳሚው ለሦስት ዓመታት በወታደራዊ ሳይንስ እና አመራር ትምህርት ሲሠለጥኑ እንደቆዩ የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።
በምርቃቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ዕጩ መኮንኖቹ በሥልጠናው ያገኙትን እውቀት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ተመራቂዎቹ አካላዊ፣ አዕምሯዊና ሥነ-ልቦናዊ ፈተናዎችን አልፈው የላቀ የጦር አመራር ክህሎትን እንደተላበሱ የገለጹት ደግሞ፤ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ጌታቸው ሃብታሙ ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X