የኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ75% በላይ መድረሱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ
16:43 25.07.2026 (የተሻሻለ: 16:44 25.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ75% በላይ መድረሱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የገጠርና ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ለማሳደግ በትኩረት በመሠራቱ፤ ሀገራዊ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ከ72.65% ወደ 75.59% ማሳደግ መቻሉን ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ አስታውቀዋል።
በሚኒስትሩ የተነሱ ተጨማሪ ቁልፍ አፈጻጸሞች፦
▪ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ84.4 ሚሊየን በላይ ደርሷል፣
▪ በበጀት ዓመቱ ከ4.85 ሚሊየን በላይ ዜጎች የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆነዋል፣
▪ የትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ43% ወደ 45% አድጓል።
ይህ የተገለጸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X