ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ስማርት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ ተጀመረ

ሰብስክራይብ

ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ስማርት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ ተጀመረ

 

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮሌጁን ግንባታ በትናንትናው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።

 

ግንባታው ሲጠናቀቅ ኮሌጁ የሚከተሉትን ጨምሮ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ሥልጠና ይሰጣል ተብሏል፦

▪በማኑፋክቸሪንግ፣

▪በአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ፣

▪በኤሌክትሮኒክስ፣

▪በኮሙኒኬሽን፣

▪በጨርቃጨርቅ፣

▪በኮምፒውተር አሃዛዊ ቁጥጥር ቴክኖሎጂ።

 

ፕሮጀክቱ “በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ወጣቶቻችንን ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት፣ ከንድፈ ሃሳብ ወደ ተግባር የሚያሸጋግር፣ አዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር የክህሎት ድልድይ የሚሆን ነው” ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0