ኬንያ በቀይ ባሕር የመርከብ ትራንስፖርት ስጋት ምክንያት በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ዙሪያ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጥሪ አቀረበች

ሰብስክራይብ
ኬንያ በቀይ ባሕር የመርከብ ትራንስፖርት ስጋት ምክንያት በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ዙሪያ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጥሪ አቀረበች

የሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕር በሚንቀሳቀሱ የንግድ መርከቦች ላይ ከሰነዘሩት ጥቃት በኋላ፤ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ አጋሮች የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስን ለመፍታት የተቀናጀ እና ሰላማዊ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው የኬንያ ጠቅላይ ካቢኔ ዋና ፀኃፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ማሳሰባቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሙዳቫዲ በአረቢያ ባሕረ ሰላጤ እና በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ መካከል በሚገኘው የባብ አል-ማንዳብ የባሕር መተላለፊያ ላይ የተደቀነው ስጋት፤ የዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የማዳበሪያ አቅርቦት ሰንሰለትን አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠንቅቀዋል።


"የሚከተለው የገቢ እቃዎች እና የኦፕሬሽን ወጪዎች መናር፤ በኬንያ እና በሰፊው ቀጣና ውስጥ የዋጋ ግሽበት ጫናን ያባብሳል ተብሎ ይጠበቃል" ማለታቸውን መገናኛ ብዙኃኑ ጠቅሰዋል።


የሀገር ውስጥ ገበያውን ከነዳጅ ዋጋ መናር ጫና ለመጠበቅ፤ ኬንያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በዘረጋችው የመንግሥት ከመንግሥት የነዳጅ ግዢ ማዕቀፍ ላይ እንደምትተማመን ገልፀዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0