ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክረምት በጎ አገልግሎት ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው
15:02 25.07.2026 (የተሻሻለ: 15:04 25.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክረምት በጎ አገልግሎት ነፃ የጤና ምርመራና ሕክምና ተጠቃሚ ሊሆኑ ነው
ሆስፒታሉ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሐሳብ ያስጀመረው መርኃ-ግብር ዋና ዓላማው በሽታዎችን ቀድሞ መከላከልና በጊዜው መለየት ሲሆን ዜጎችም ቀድመው የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበትን ጠቃሚ ዕድል እንደሚፈጥር የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አስታውቀዋል።
በመርኃ-ግብሩ ከመደበኛ ምርመራ ባሻገር የቀዶና የስፔሻሊቲ ሕክምና፣ ሲቲ ስካን፣ ኤምአርአይ ምርመራዎች እንደሚሰጡ ተገልጿል።
በዚህ የክረምት ተነሳሽነት ከሕክምና አገልግሎት በተጨማሪ፤ የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እና የማዕድ ማጋራትም ተካቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X