- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከአእምሮአዊ ጥገኝነት ወደ አፍሪካዊ ሉዓላዊነት፦ የበርሊን ጉባኤን ጥቁር ጥላ ማጥፋት

ከአእምሮአዊ ጥገኝነት ወደ አፍሪካዊ ሉዓላዊነት፦ የበርሊን ጉባኤን ጥቁር ጥላ ማጥፋት
ሰብስክራይብ
“በግድግዳው ላይ የተሰነጠቁ ስንጥቆችን ለማከም ሲሚንቶ ለጥፈን ለማስተካከል እንሞክር ይሆናል፤ ነገር ግን ዋናው ችግር ያለው በሕንጻው መሠረት ላይ ነው። … ወደፊት ወዴት እየሄድን እንዳለን ለመረዳት፣ ይህ የበርሊን ጉባኤ መርዝ አእምሮአዊ እንደሆነ መገንዘብ አለብን። ስለዚህ አፍሪካዊ ማዕከላዊነት ዓለምን የምንጋፈጠው በሌሎች መለኪያ ሳይሆን በራሳችን አፍሪካዊ መለኪያና ማንነት ላይ ቆመን መሆን እንዳለበት ያሳስበናል።" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና 'ዲቨሎፒንግ አፍሪካ ? ኔው ሆራይዘንስ ዊዝ አፍሮሴንትሪሲቲ' መጽሐፍ ደራሲ ሌሄሳ ሞሎይ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በተጨማሪም "ሰው ሰራሽ የአፈር ድንበሮች ማንነታችንንና አንድነታችንን ሊገድቡት አይችሉም። ድንበሮችን እንደ ማደናቀፊያ ከመመልከት ይልቅ በሚያስተስሩንና በሚያበልጡን እሴቶቻችን ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን። አፍሪካዊ ማዕከላዊነት እንደገና የምንገነባበት ዋናው መሠረታችንና ማዕከላችን ነው።" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ደራሲ ከሆኑት ከሌሄሳ ሞሎይ (ዶ/ር) ጋር፣ አፍሪካ ከበርሊን ጉባኤ አእምሮአዊና ድንበራዊ ጥገኝነት ወጥታ እውነተኛ ፓን-አፍሪካዊ አንድነትንና አፍሪካዊ ማዕከላዊነትን እንዴት ልታረጋግጥ እንደምትችል በስፋት እንወያያለን።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0