የፌዴራል መሶብ አገልግሎት ለሦስት ዓመት የሚመራበትን ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረገ
18:30 24.07.2026 (የተሻሻለ: 18:34 24.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የፌዴራል መሶብ አገልግሎት ለሦስት ዓመት የሚመራበትን ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረገ
የፌደራል፣ የከተማ አስተዳደሮች እና የክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ በስትራቴጂክ ዕቅዱ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ቁልፍ የፍኖተ ካርታው ነጥቦች፦
▪ ትግበራው ከ2019 እስከ 2021 ዓ.ም ይቆያል።
▪ አገልግሎቱ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ ይሆናል።
▪ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እቅድን መነሻ ያደረገ ነው።
መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረጉት የመሶብ አገልግሎት ማዕከላት፤ አሁን ላይ በሁሉም ክልሎች 100 ደርሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X