የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሩሲያ አትሌቶችን እገዳ ለማራዘም ያሳለፈው ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም - የሕግ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaየዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሩሲያ አትሌቶችን እገዳ ለማራዘም ያሳለፈው ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም - የሕግ ባለሙያ
የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሩሲያ አትሌቶችን እገዳ ለማራዘም ያሳለፈው ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም - የሕግ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.07.2026
ሰብስክራይብ

የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሩሲያ አትሌቶችን እገዳ ለማራዘም ያሳለፈው ውሳኔ ሕጋዊ መሠረት የለውም - የሕግ ባለሙያ

 

"የሩሲያ እና የቤላሩስ አትሌቶች በግጭቶች ውስጥ የተሳተፉ ሀገራት አትሌቶች በስፖርት ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፉ የሚከለክል ምንም ዓይነት ሕግ ወይም ድንጋጌ በሌለበት አግባብ ባልሆኑ እና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ከውድድር ታግደዋል" ሲሉ ቱርካዊዉ የዓለም አቀፍ ሕግ እና ግንኙነት ባለሙያ ሀሰን ኬኒ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

የሩሲያ እና የቤላሩስ አትሌቶች እገዳ በሕጋዊ ወይም በስፖርታዊ መመዘኛዎች ላይ ያልተመሠረተ እና የፖለቲካ አድልዎ መግለጫ እንደሆን ባለሙያው በአፅንዖት ተናግረዋል። በዚህም የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፖለቲካ እና ስፖርት መደባለቅ የለባቸውም ብሎ በግልጽ ያስቀምጠውን የኦሎምፒክ ቻርተር ጥሷል ብለዋል።

የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ በሩሲያ እና በቤላሩስ አትሌቶች ላይ የተጣሉት ገደቦች እንዲነሱ ሰኔ 30 ያሳለፈውን ውሳኔ ለመተግበር ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የድርጅቱ ገለልተኝነት እና የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ትችት ተነስቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0