ዩኔስኮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጂኦ ፖርክን ገመገመ
17:09 24.07.2026 (የተሻሻለ: 17:14 24.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩኔስኮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጂኦ ፖርክን ገመገመ
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባሕል ድርጅት ልዑክ በጂኦ ፖርኩ ከሐምሌ 14-16 2018 ዓ.ም ያካሄደውን የአካል ምልከታ አጠናቋል።
የቡድኑ ተልዕኮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጂኦ ፖርክ በዩኔስኮ እውቅና መዝገብ ውስጥ ለመስፈር እያሟላቸው የሚገኙ መስፈርቶችን መገምገም ነው።
ጂኦ ፓርኩ የድርጀቱን ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያሟላ በርካታ ሥራ መሠራታቸውን የጠቀሰው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴር፤ ሥፍራው በእውቅና መዝገቡ ውስጥ ይገባል ብሎ እንደሚጠብቅ በማኅበራዊ ገጹ ባጋራው መረጃ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X