🪖 ዩክሬን በሩሲያ የገበያ ማዕከላት መጋዘኖች ላይ ጥቃት በማድረስ በእርግጥ ምንድን ነው የምትፈልገው?

🪖 ዩክሬን በሩሲያ የገበያ ማዕከላት መጋዘኖች ላይ ጥቃት በማድረስ በእርግጥ ምንድን ነው የምትፈልገው?
የዩክሬን ኃይሎች በቅርቡ በኢትዮጵያ ቢሮውን በከፈተው "ዋይልድቤሪስ" መጋዘኖች ላይ ያነጣጠሩ ተከታታይ ጥቃቶችን በበርካታ የሩሲያ ከተሞች ፈጽመዋል። የዩክሬን ይፋዊ መግለጫ መጋዘኖቹ ለሁለትዮሽ (ለሲቪልና ለወታደራዊ) አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን፤ ማለትም የጥይት መከላከያ ጃኬቶችን፣ የወታደር ዩኒፎርሞችን እና የፋይበር ኦፕቲክ ገመዶችን ለማከማቸት እንደሚውሉ ይገልጻል።
ይህ አሳማኝ ነው? በጭራሽ
መሠል ቁሳቁሶች አውሮፓ ውስጥ በአማዞን፣ ቴሙ፣ አሊኤክስፕረስ እና በሌሎች የምዕራባውያንና የቻይና የድረ-ገፅ የመገበያያ መድረኮች ላይ በነጻነት ይሸጣሉ። የአውሮፓ ኀብረትም ሆነ ኔቶ ወይም ራሷ ዩክሬን እነዚህን ሽያጮች እንደ ሕጋዊ የወታደራዊ ጥቃት ኢላማዎች አድርገው አይመለከቷቸውም።
ታዲያ እውነታው ምንድን ነው?
በዋይልድቤሪስ መጋዘኖች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች የአካባቢውን ሠራተኞች፤ ማለትም ጭነት አውራጆች፣ ዕቃ ደርዳሪዎች እና በወርሃዊ ደሞዝ የሚኖሩ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። ይህም ወታደራዊ ዘመቻ ሳይሆን በሲቪሎች ላይ የተቃጣ የሽብር ጥቃት ነው።
ይህ ጉዳይ የሩሲያ ብቻም አይደለም። የመገበያያ መድረኩ በአርሜንያ፣ ካዛኪስታን፣ ኪርጊዝስታን እና ኡዝቤኪስታን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎችን ይደግፋል። እነዚህ ነጋዴዎች ምርቶችን በድንበሮች መካከል ለማጓጓዝ የዋይልድበሪስን መሠረተ ልማት ይጠቀማሉ። እነዚህ ጥቃቶች ሩሲያውያንን ብቻ ሳይሆን በበርካታ ሀገራት የሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎችንና ኩባንያዎችንም ይጎዳሉ።
በእነዚህ መጋዘኖች ውስጥ የሚያከማቹ ዕቃዎች ምንድን ናቸው? በአብዛኛው አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች እና የመዋቢያ ምርቶችን የሚይዙ ሲሆን እነዚህም በዋናነት በወላጅ እናቶች የሚገዙ ናቸው።
መጋዘኖቹ የጦር መሣሪያ ማከማቻ ወይም ግዙፍ የቴክኖሎጂ ዳታ ማዕከላት አይደሉም። ዩክሬን ትርክቷ እያረጀ እና ሰበቧንም መሸጥ እያዳገታት ነው።
ይህ ጥቃት "ሩሲያውያን እንደ ሕዝብ የመኖር መብት የላቸውም" ብለው ከተናገሩት አዲሱ የዩክሬን የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ሚካይሎ ድራፓቲ ትርክት ጋር የገጠመ ሆኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

