የኢትዮጵያ የቡና ምርት በጎርጎሮሳውያኑ የ2026/27 የበጀት ዓመት ከፍተኛ እድገት ያስመዘግባል - ሪፖርት

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ የቡና ምርት በጎርጎሮሳውያኑ የ2026/27 የበጀት ዓመት ከፍተኛ እድገት ያስመዘግባል - ሪፖርት

🫘 የአሜሪካ የግብርና ሚኒስቴር የውጭ ግብርና አገልግሎት ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ የሀገሪቱ የቡና ምርት ከባለፈው ዓመት (2025/2026) ከ500 ሺህ ከረጢት (አንድ ከረጢት 60 ኪ.ግ) ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቶ 12.1 ሚሊዮን ከረጢት ደርሷል።

ለዚህ ከፍተኛ ምርት እንደ ዋና ምክንያት የተጠቀሰው ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የቡና ተክል በከፍተኛ ምርት በሚሰጡና በሽታን በሚቋቋሙ አዳዲስ ዝርያዎች ለመተካት የተደረገው ጥረት መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል።

በሪፖርቱ ኢትዮጵያን በሚመለከት የተጠቀሱ ዋና ዋና መረጃዎች

በምርቱ ማደግ ምክንያት ወደ ውጭ የሚላከው የቡና መጠን ወደ 7.1 ሚሊዮን ከረጢት ከፍ ይላል፡፡

ከ5 ሚሊዮን ከረጢት በላይ የሚሆነው ምርት ደግሞ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ይውላል።

ኢትዮጵያ በአረቢካ ቡና ምርቷ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከብራዚል እና ኮሎምቢያ በመቀጠል 3ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

በአጠቃላይ ቡና አምራችነት ደረጃ ከብራዚል፣ ቪዬትናም እና ኮሎምቢያ በመቀጠል 4ኛ ደረጃ ትገኛለች፡፡

በአገር ውስጥ ከፍተና የቡና ፍጆታ ምክንያት የጥሬ ቡና ወጪ ንግዷ ከ800 ሺህ ቀረጢት በላይ ቀንሶ ወደ 6.9 ሚሊዮን ዝቅ ብሏል።

ኢትዮጵያ በአዲሱ የ2019 በጀት ዓመት 550 ሺህ ቶን ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለማግኘት ማቀዷን ግብርና ሚኒስቴር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0