ሩሲያ ለግብፅ የአቢዮት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈች፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ወዳጅነት አጉልታለች
17:40 23.07.2026 (የተሻሻለ: 17:44 23.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለግብፅ የአቢዮት ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፈች፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ወዳጅነት አጉልታለች
የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ቫለንቲና ማትቪየንኮ እንደገለፁት፣ በሞስኮ እና በካይሮ መካከል ያለው አጠቃላይ አጋርነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነው።
በንግድ፣ በኢኮኖሚ እና በሰብአዊ መስኮች ትብብርን ማሳደግ እንዲሁም
በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ጥረቶችን ማስተባበር ናቸው።
“ሰላም፣ ደህንነት እና ብልፅግና” ሲሉም መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
ማትቪየንኮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በሁለትዮሽም ሆነ በባለብዙ ወገን ደረጃ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
የግብፅ የአቢዮት ቀን የሚከበረው እ.ኤ.አ ሐምሌ 23 ነው፡፡ በዚህ ቀን እ.ኤ.አ በ1952 በገማል አብደል ናሰር በተመራው አብዮት ንጉሥ ፋሩቅ አንደኛ ከሥልጣን ተወግደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X