ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 92.9 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
15:45 23.07.2026 (የተሻሻለ: 15:54 23.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 92.9 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
የኩባንያው ይህ ትርፍ፣ ባለፈው በጀት (በ2024/25) ከተገኘው 63 ቢሊዮን ብር የ47.5 ብልጫ እንዳለው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።
ኩባንያው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 215.8 ቢሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱንም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል። ገቢው በባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት (ሰኔ 2025) ከተገኘው 162 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ የ33.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው በዛሬ ዕለት ባቀረቡት ዓመታዊ ሪፖርታቸው ላይ አብራርተዋል።
ገቢው በዋናነት ከድምጽ፣ ከዳታ እና ከተለያዩ የአገልግሎት ሽያጮች የተገኘ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ በኩባንያው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዳታ የተገኘው ገቢ ከድምጽ ከተገኘው ስለመብለጡም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X