በትግራይ የጣለው ከባድ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት አለፈ፤ ሰብሎች ላይ ጉዳት ደርሷል
14:05 23.07.2026 (የተሻሻለ: 14:14 23.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በትግራይ የጣለው ከባድ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት አለፈ፤ ሰብሎች ላይ ጉዳት ደርሷል
በማዕከላዊ ዞን ወረዳ ቀይሕ ተኽሊ ዶክተር አታኽልቲ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር፣ ለሁለት ሠዓታት ያለማቋረጥ የዘነበው በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ በሰብሎች እና በመስኖ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በተመሳሳይ በዞኑ ወረዳ አሕፈሮም ሴሮ ቀበሌ የዘነበው ከባድ ዝናብም በአዝርእት እና በአትክልት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ገልጿል።
በሌላ በኩል የትግራይ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ጥበቃ ቢሮ ሰኞ ዕለት ባወጣው መረጃ፣ በክልሉ ከሚገኙ 600 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት መካከል 176 በሚሆኑት እስካሁን የክረምት ዝናብ እንዳልዘነበ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X