የኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረበት በ8.3 በመቶ አደጎ 90.1 ሚሊዮን ደርሷል – ዋና ሥራ ስፈጻሚ

ሰብስክራይብ

የኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት ከነበረበት በ8.3 በመቶ አደጎ 90.1 ሚሊዮን ደርሷል – ዋና ሥራ ስፈጻሚ

ፍሬሕይወት ታምሩ ይህን የተናገሩት፣ የኩባንያውን የ2025/26 በጀት ዓመት እና የቀጣዩ አድማስ የ3 ዓመታት ስትራቴጂ የመጀመሪያ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርትን ባቀረቡበት ወቅት ነው።

“ኢትዮ ቴሌኮም አሁንም የዲጂታል ኢትዮጵያ ነርቭ ሲስተም ሆኖ ቀጥሏል” ሲሉ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በሪፖርታቸው የጠቀሷቸው ዋና ዋና ቁጥራዊ መረጃዎች፦

ኩባንያው በፊክስድ ብሮድባንድ አገልግሎት ከፍተኛ የሆነ የአንድ ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ቁጥር ላይ ደርሷል፡፡

በበጀት ዓመቱ ብቻ ቢሊዮን ብር ገደማ ኢንቨስትመንት አካሂዷል፡፡

በቴሌብር የ4.1 ትሪሊዮን ብር ዋጋ ያለው የገንዘብ ዝውውር ተደርጓል፡፡

አጠቃላይ የቴሌብር ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ60 ሚሊዮን ተሻግሯል፡፡

በቴሌብር በቀን እስከ 11 ቢሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ ዝውውር ይደረጋል፡፡

የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት በ12.71 ሚሊዮን ጨምሯል፡፡

ከ40 ሚሊዮን ዶላር በላይ የምንዛሬ ገንዘብ በሬሚታንስ መልክ ተገኝቷል፡፡

በስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ የተቀረጸ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0