የሩሲያ ጦር በዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ላይ ሌላ የሌሊት ጥቃት ፈጸመ - የመከላከያ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ጦር በዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ላይ ሌላ የሌሊት ጥቃት ፈጸመ - የመከላከያ ሚኒስቴር

▫ በኦዴሳ ወደብ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ለማውረድ እና ለማከማቸት የሚያገለግሉ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የዩክሬን ጦር ኃይሎች የሚገለፈሉባቸው የነዳጅ እና የቅባት ታንከሮችን ላይ ውድመት ደርሷል::

▫ በባሕር ማቋረጫ መስመር ላይ (ከኦዴሳ በስተደቡብ ምሥራቅ 15 ኪ.ሜ እና 53 ኪ.ሜ ርቀት ላይ)፣ ለዩክሬን ጦር ኃይሎች መሣሪያዎችን ወደ ኦዴሳ እና ቸርኖሞርስክ ወደቦች ያጓጉዙ የነበሩ አንድ የጭነት መርከብ እና ሌላ የጅምላ ጭነት መርከብ ዒላማ ተደርገዋል፡፡

▫ በኦዴሳ ከተማ፣ ወታደራዊ መሣሪያዎችን ለማከማቸት ያገለግል የነበረ የአንድ ትልቅ አቅርቦት ኩባንያ የሎጂስቲክስ ማዕከል ተመቷል፡፡

▫ በተጨማሪም፣ ኮቫልዮቭካ በተባለች መንደር አካባቢ (ከኦዴሳ በስተሰሜን ምዕራብ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ)፣ የኔፕቱን-2 የባሕር ዳርቻ ሚሳይል ሥርዓት ተመቷል። ሁለት ሚሳይል ማስወንጨፊያዎች እና አንድ የማጓጓዣና የመጫኛ ተሽከርካሪ ተደመስሰዋል።

ቪዲዮ፦ በጥቁር ባሕር በዩክሬን መርከቦች ላይ የተፈጸመ ጥቃት

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0