የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት የኃይል ማመንጫ ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ የኮንክሪት ሙሌት መጠናቀቁ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት የኃይል ማመንጫ ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ የኮንክሪት ሙሌት መጠናቀቁ ተዘገበ

የኮይሻ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ የስትራክቸራል ኮንክሪት ሙሌት ሥራ በስኬት መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ የሲቪል መሐንዲስ ይታገሱ አያሌው ለሀገር ውስጥ የመንግሥት ሚዲያ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱን በተመለከተ በመሃንዲሱ የተጠቀሱ ዋና ዋና መረጃዎች፦

ከ7.725 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የአርማታ ሙሌት ውስጥ ከ6.2 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ተጠናቋል፡፡

አሁን ላይ የግድቡ ቁመት 136 ሜትር የደረሰ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አጠቃላይ ቁመቱ 201 ሜትር ይደርሳል።

ግድቡ እያንዳንዳቸው 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ 6 ተርባይኖች (በአጠቃላይ 1,800 ሜጋ ዋት) ይኖሩታል፡፡

የኤሌክትሮ-መካኒካል ተከላ ክፍሎች በምርት ሂደት ላይ ይገኛሉ።

የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ግንባታ የስትራክቸራል አርማታ ሙሌት ሥራ 45 በመቶ ደርሷል።

ፕሮጀክቱ ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ከፍተኛ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ከመፍጠሩ ባሻገር ሲጠናቀቅ የሚፈጥረው ሰው ሠራሽ ሐይቅ በ'ገበታ ለሀገር' መርሃ-ግብር ለታቀዱ የአካባቢው የቱሪዝም ልማቶች ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0