በድሬዳዋ ዘላቂ የከተሞች የትምህርት ቤት ምገባ ሞዴል ይፋ ተደረገ

ሰብስክራይብ

በድሬዳዋ ዘላቂ የከተሞች የትምህርት ቤት ምገባ ሞዴል ይፋ ተደረገ

በከተማዋ የሚገኙ ተማሪዎችን የአመጋገብ፣ የጤና እና የትምህርት አቀባበል አቅም ለማሻሻል ያለመውን ይህን ሞዴል ዩኒሴፍ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ምገባ ኢኒሼቲቭ ጋር በመተባበር አስጀምሮታል፡፡

የፕሮግራሙ ቁልፍ ተግባራት፦

ለአካባቢ ጥበቃና ለምግብ ደህንነት ትኩረት በመስጠት ለ10 ሺህ ያህል ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ ያዘጋጃል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ለፕሮግራሙ የሚሆን 18 ሄክታር መሬት ለምግብ የሚሆኑ አትክልትና እህሎች ማመርቻ እንዲሆን መድቧል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከከተማው የካፒታል ታክስ ገቢ 3% ለትምህርት ቤት ምገባ መርሃ-ግብር ለመመደብ ቃል ገብቷል።

ድሬዳዋን ለሌሎች ከተሞች ተመራጭ አርዓያ ለማድረግ እንደሚሠራ የፌደራልና የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0