በኢነርጂ ዘርፉ ላይ ጫና ቢኖርም የሩሲያ ኢኮኖሚ መረጋጋቱን አስጠብቆ ቀጥሏል - ፑቲን
14:34 22.07.2026 (የተሻሻለ: 14:44 22.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በኢነርጂ ዘርፉ ላይ ጫና ቢኖርም የሩሲያ ኢኮኖሚ መረጋጋቱን አስጠብቆ ቀጥሏል - ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሰጧቸው ሌሎች መግለጫዎች፦
በነዳጅ እና ጋዝ እንዲሁም ከነዳጅ እና ጋዝ ውጭ በሚገኙ ገቢዎች በመታገዝ የሩሲያ በጀት በሰኔ ወር የ2.5 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የበጀት ትርፍ አስመዝግቧል፡፡
የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት ዕድገት በግንቦት ወር 0.3% የደረሰ ሲሆን፣ የዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ዕድገት ደግሞ 0.2% ደርሷል፡፡
ከነዳጅና ጋዝ ውጭ ያሉ የበጀት ገቢዎች በሁለተኛው ሩብ ዓመት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሩብ (25%) አድገዋል፡፡
በነዳጅ ገበያው ላይ የታዩ መስተጓጎሎች ጊዜያዊ በመሆናቸው በጠቅላላው ኢኮኖሚ ላይ ጎልቶ የሚታይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡
አዲስ የኢንቨስትመንት ዑደት መጀመር ከሩሲያ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ሆኗል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X