"የራሳችን የሆነውን ነው እየጠየቅን ያለነው" - ናይጄሪያዊቷ ባለሥልጣን የባህል ቅርሶችን ስለማስመለስ
13:54 22.07.2026 (የተሻሻለ: 14:04 22.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"የራሳችን የሆነውን ነው እየጠየቅን ያለነው" - ናይጄሪያዊቷ ባለሥልጣን የባህል ቅርሶችን ስለማስመለስ
"የምዕራቡ ዓለም የበላይ እንደሆነ ስለተሰማው" በቅኝ ግዛት ዘመን የተወሰዱ ቅርሶች አሁን በ"መንግሥት፣ ተቋማት እና ግለሰቦች" የተቀናጀ ጥረት እየተመለሱ ይገኛሉ ሲሉ የብሔራዊ ቤተ-መዘክሮች እና ቅርሶች ኮሚሽን አስተዳደራዊ ኃላፊ ዋሳ ገርትሩድ ሞቡኑባታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የባህል ቅርሶችን ማስመለስ ቅርሶቹን በመስታወት ሣጥን ስለማስቀመጥ አይደለም፤ ይልቁን የአፍሪካ የፈጠራ ኢኮኖሚ በአሁኑ ወቅት የሚጎድለውን መሠረታዊ የባሕል ሀብት የመመለስ ጉዳይ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
የአእምሯዊ ሥራ እሴት ለማሳደግ የአፍሪካ ሀገራት በሚከተሉት ላይ ኢንቨስት ማድረግ አለባቸው፦
ዩኒቨርሲቲዎች፣
የምርምር ተቋማት እና
የፈጠራ ዘርፎች፡፡
"እነዚህን የባሕል ሀብቶች ማጣት ረቂቅ የፅንሰ-ሐሳብ ክርክር አይደለም። ይልቁንም ራስን የማወቅ እና የማንነት ቀጣይነት ያለው ጉዳይ ነው። እኛ የቅርሶቻችን ባለቤቶች ነን።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X