የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማጎልበት የተገነባው የሶማሌ ክልል አዲሱ የኢኖቬሽን ማዕከል

ሰብስክራይብ

የወጣቶችን የፈጠራ ችሎታና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ለማጎልበት የተገነባው የሶማሌ ክልል አዲሱ የኢኖቬሽን ማዕከል

ክልሉ ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞውን የሚያፋጥንና የወጣቶችን የቴክኖሎጂና የፈጠራ አቅም የሚያሳድግ ዘመናዊ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ማዕከል በትናንትናው ዕለት በይፋ አስመርቋል።

የኢኖቬሽን ማዕከሉ ዋና ዋና አገልግሎቶች፦

የወጣቶችን የፈጠራ ክህሎትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ፣

የዲጂታል ክህሎት ማደጊያ ሥልጠናዎችን መስጠት፣

ለወጣቶች ከቴክኖሎጂ ጋር የተጣጣሙ የሥራ ዕድሎችን ማመቻቸት

ለአነስተኛ እና ጀማሪ የንግድ ተቋማት አገልግሎት መስጠት፣

የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፣

ለሳይንሳዊ ምርምሮችና ለዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያነት አገልግሎት መስጠት ናቸው።

ማዕከሉ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች የሚታዩበት፣ ሥልጠናዎች የሚሰጡበት እና የምክክር መድረኮች የሚካሄዱበት እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0