አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን ቀራፂ መሆን አለባት - ሴኔጋላዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን ቀራፂ መሆን አለባት - ሴኔጋላዊ ባለሙያ

በሴኔጋል ሼክ ሀሚዱ ካኔ ዲጂታል ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር ሰይዲና ሙሳ ንዲያዬ ፣ አፍሪካ ከአዲሱ የዲጂታል ቅኝ ግዛት ስጋት እንዴት መውጣት እንዳለባት አብራርተዋል።

“አደጋው የሚፈጠረው የአፍሪካ ሀገራት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን አብረው የሚቀርፁ፣ የሚያመርቱ እና ባለቤቶች ከመሆን ይልቅ የቋሚ ተጠቃሚነት እና የመረጃ አቅራቢነት ሚና ላይ ብቻ ሲወሰኑ ነው” ሲሉ ባለሙያው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ትብብሮች አስፈላጊ ቢሆኑም፣ አፍሪካ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ አቅሟን ማሳደግ፣ ስትራቴጂካዊ መረጃዎቿን መጠበቅ እና የምርምር ተቋሞቿን ማጠናከር እንዳለባት ባለሙያው አሳስበዋል።

አፍሪካ የመረጃ እና የባለሙያዎች አቅራቢ ብቻ ሆና ከመቅረት ይልቅ ከሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚፈጠረውን እሴትና ጥቅም በፍትሐዊነት መጋራት ይኖርባታል ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0