የኢትዮጵያ 21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በደቡብ ሱዳን የነበረውን ተልዕኮ ለ23ኛ ሻለቃ አስረከበ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ 21ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በደቡብ ሱዳን የነበረውን ተልዕኮ ለ23ኛ ሻለቃ አስረከበ

ሰላም አስከባሪ ሻለቃው በደቡብ ሱዳን የነበረውን የተባበሩት መንግሥታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ አጠናቆ ለ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የሰንደቅ ዓላማና የአርማ ማስረከብ ስነ-ስርዓት አከናውኗል።

የአስረካቢው 21ኛ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ ሻለቃቸው በያምቢዮ፣ ፓዙ እና ዱሩፒ ካምፖች ሰፊ ቀጣና በመሸፈን ፈታኝ ግዳጆችን በብቃት መወጣቱን እና ከማኅበረሰቡ ጋር በነበረው መልካም ግንኙነት ምስጋና ማግኘቱን ገልጸዋል።

የተረካቢው 23ኛ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሀይሉ ተረፈ በበኩላቸው በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ማዕከል ያገኘውን ሙያዊ አቅም እና ከአስረካቢው የወሰደውን ተሞክሮ በመጠቀም ለደቡብ ሱዳን ሰላምና ልማት በተባበሩት መንግሥታት መርሆች መሠረት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተመድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዌስተርን ኢኳቶሪያ ስቴት አስተዳዳሪዎች፣ የአካባቢው የፀጥታ አካላት እና የልዩ ልዩ ሀገራት ሰላም አስከባሪዎች መገኘታቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0