ኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የምታስተናግደው የአፍሪካ ዞን 4.4 የቼስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የምታስተናግደው የአፍሪካ ዞን 4
ኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የምታስተናግደው የአፍሪካ ዞን 4 - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.07.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ለ3ኛ ጊዜ የምታስተናግደው የአፍሪካ ዞን 4.4 የቼስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

በውድድሩ 36 ስፖርተኞች ስድስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ወክለው የሚሳተፉ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በ5 ወንድ እና በ5 ሴት ተወዳዳሪዎች እንደምትሳተፍ የኢትዮጵያ ቼስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ለቼስ ሻምፒዮናው ልዑካን ቡድኖቻቸውን ወደ አዲስ አበባ የላኩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት

የኢትዮጵያ፣

ጅቡቲ፣

ማዳጋስካር፣

ሶማሊያ፣

ኡጋንዳ እና

ኬንያ

ከሻምፒዮናው ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ ዳኞች ሥልጠና የሚሰጥ ሲሆን፤ የዓለም የቼስ ቀን እና የአፍሪካ ቼስ ኮንፌዴሬሽን 50ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልም ተያይዞ እንደሚከበር ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

በመጪው ሰኞ የአፍሪካ ቼስ ኮንፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ጉባኤው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ከመገምገሙ ባሻገር ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት ኮንፌዴሬሽኑን የሚመሩ አዳዲስ አመራሮች ምርጫ ያካሂዳል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0