ኢትዮጵያ እና ማልዲቭስ የቀጥታ በረራ ለማስጀመር የሚያስችላቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እና ማልዲቭስ የቀጥታ በረራ ለማስጀመር የሚያስችላቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ማልዲቭስ የቀጥታ በረራ ለማስጀመር የሚያስችላቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.07.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ማልዲቭስ የቀጥታ በረራ ለማስጀመር የሚያስችላቸውን የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ

የሁለቱን ሀገራት የአቪዬሽን ትስስር ለማጠናከር ያለመውን የሁለትዮሽ ስምምነት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ አበራ እና የማልዲቭስ የትራንስፖርትና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር ሞሐመድ አሜን ተፈራርመውታል።

በዚህም ማልዲቭስ ከአፍሪካ አገራት ጋር የአየር አገልግሎት ስምምነት ስትፈራረም ኢትዮጵያ ከግብጽ፣ ሞሪሺየስ፣ ሩዋንዳ፣ ሲሸልስ እና ደቡብ አፍሪካ በመቀጠል 6ኛዋ አገር ሆናለች።

ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ማልዲቭስ ማሌ የቀጥታ በረራ እንዲጀምር መንገድ የሚከፍት ሲሆን፤ የማልዲቭስ ብሔራዊ አየር መንገድም ወደ ኢትዮጵያ በረራዎችን ለማድረግ ያስችለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማልዲቭስ በመነሳት ወደ አስያ እና ፓሲፊክ አገራት የበረራ መስመሩን ለማስፋፋት የሚያስችለውን ዕድል ይሰጠዋል።

በተጨማሪም ስምምነቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የቱሪዝም፣ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0