ኢራን ለአሜሪካ ጥቃቶች በሰጠችው የአጸፋ ምላሽ በጆርዳን፣ ባሕሬን እና ኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ማዕከላት ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች - መገናኛ ብዙኃን
12:15 21.07.2026 (የተሻሻለ: 12:24 21.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢራን ለአሜሪካ ጥቃቶች በሰጠችው የአጸፋ ምላሽ በጆርዳን፣ ባሕሬን እና ኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ማዕከላት ላይ ጥቃት መፈጸሟን ገለጸች - መገናኛ ብዙኃን
መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኮርፕስ ካወጣቸው መግለጫዎች የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
በባሕሬን፣ በዋናው የአማዞን የመረጃ ማዕከል መሠረተ ልማት ላይ በሌሊት ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ አንድ ራዳር እና የፔትሪዮት የአየር መከላከያ ሥርዓት ወድመዋል፡፡
በኩዌት፣ የረጅም ርቀት ራዳሮች፣ የሳተላይት መገናኛ ሥርዓቶች እና የፀረ-ሚሳይል መከላከያ ራዳሮች ተመተዋል፤ በአህመድ አል-ጃበር የአሜሪካ የአየር ኃይል ማዕከል በርካታ ራዳሮች እና የፓትሪዮት ፀረ-ሚሳይል መከላከያ ሥርዓቶች ወድመዋል፡፡
በጆርዳን፣ በአንድ የአሜሪካ የጦር ማዕከል ውስጥ የፀረ-ሚሳኤል መከላከያ ራዳር እና አንድ ኤፍ-15 ተዋጊ ጄት ወድመዋል፡፡
በሆርሙዝ ወሽመጥ በደረሱ ፍንዳታዎች ሳቢያ ሁለት የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በእሳት ተቃጥለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X