በ8 ክልሎች ከ41 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ ተጀመረ – ጤና ሚኒስቴር
11:55 21.07.2026 (የተሻሻለ: 12:04 21.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በ8 ክልሎች ከ41 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ ተጀመረ – ጤና ሚኒስቴር
ዘመቻው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ 401 ወረዳዎች ውስጥ የሚከናወነው ሲሆን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በይፋ መበሰሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
ዘመቻው ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸውን 7 የተቀናጁ የጤና አገልግሎቶችን ያካተተ ነው፦
የትራኮማ፣ የዝሆኔ እና የፎከት የጅምላ መድኃኒት እደላ፣
የዓይን ጤና ምርመራ፣
የወባ ምርመራና ህክምና፣
የቲቢ (TB) ምርመራ እና
የማሕፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ፡፡
ይህ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ዘመቻ “ቴልኮም ፕላስ” በሚል ሥያሜ ከሐምሌ 13 እስከ 24/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X