ደቡብ አፍሪካ የአገር ውስጥ የመከላከያ ኢንዱስትሪዋን ለማሳደግ ያለሙ አሠራሮችን ዘረጋች - ሚኒስትር
11:25 21.07.2026 (የተሻሻለ: 11:34 21.07.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ የአገር ውስጥ የመከላከያ ኢንዱስትሪዋን ለማሳደግ ያለሙ አሠራሮችን ዘረጋች - ሚኒስትር
ሀገሪቱ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ከዓለም አቀፉ የመከላከያ ገበያ ጋር ለማስተሳሰር የተወሰኑ ጣልቃ-ገብነቶችን በመተግበር ላይ ትገኛለች ሲሉ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ፓርክስ ታው በ"ዲፌንስ ኢንዱስትሪ ለኮትላ" መድረክ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል።
የመከላከያ ምርቶች ወጪ ንግድን ለማሳደግ ከተወሰዱት ቁልፍ እርምጃዎች መካከል፦
🟠የእሴት ሰንሰለት ትስስር፦ የውጭ ኢንቨስተሮች የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን በሀገር ውስጥ የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ እንዲያሳተፉ ግዴታ ተጥሏል፡፡
🟠ልዩ የመድን አገልግሎት፦ የኤክስፖርት ክሬዲት ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን የመከላከያ ፕሮጀክቶችን ዋስትና ለመስጠት የተለዩ አሠራሮችን ዘርግቷል፡፡
🟠የታለመ የገንዘብ ድጋፍ፦ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን የሀገር ውስጥ የመከላከያ ማኑፋክቸሪንግን ለማስፋፋት የተለየ የፋይናንስ ፈንድ አቋቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X