የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይት ጀመሩ - ኮሚሽኑ
10:52 21.07.2026 (የተሻሻለ: 10:54 21.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች በተመደቡላቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይት ጀመሩ - ኮሚሽኑ
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው ብሔራዊ የምክክር ጉባኤ ወደ ዋናው የውይይት ምዕራፍ መሸጋገሩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ማሕሙድ ድሪር በሰጡት መግለጫ, ከ4,000 በላይ ተሳታፊዎች በኮሚሽኑ በተለዩት 8 ዋና ዋና ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ በተመደቡባቸው ቡድኖች አማካኝነት ዝርዝር ውይይት መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ተሳታፊዎች በ8 ዋና ዋና የሥራ ቡድኖች (እያንዳንዳቸው 500 አባላት) ከተደራጁ በኋላ፥ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ለማድረግ ይቻላል ዘንድ አጠቃላይ ሂደቱ ወደ 80 ንዑሳን ቡድኖች (እያንዳንዳቸው 50 አባላት) ተከፍለው ምክክሩ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
ውይይቱን በብቃት ለመምራት 160 ልምድ ያላቸው አመቻቾች እንዲሁም የውይይቱን ሂደት በትክክል ለመመዝገብ 256 ቃለ-ጉባኤ ያዦች መመደባቸውንም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X