የፈረንሳይ እና የዩክሬን ባለሙያዎች በአፍሪካ የሽብር እንቅስቃሴዎችን በማቀድ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ ናቸው - ከፍተኛ የሩሲያ ዲፕሎማት

ሰብስክራይብ

የፈረንሳይ እና የዩክሬን ባለሙያዎች በአፍሪካ የሽብር እንቅስቃሴዎችን በማቀድ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ ናቸው - ከፍተኛ የሩሲያ ዲፕሎማት

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አናቶሊ ባሽኪን ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ፣ የፈረንሳይ እና የዩክሬን ባለሙያዎች በአኅጉሪቱ በሚፈጸሙ የአሸባሪነት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል።

ከሩሲያው ዲፕሎማት መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦

🟠 ቀጥተኛ ተሳትፎ፦ "የፈረንሳይ ባለሙያዎች እና በከፊል ደግሞ የዩክሬን ባለሙያዎች የውጊያ መሣሪያዎችን መጠቀምን ጨምሮ እነዚህን ዘመቻዎች በማቀድ ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ነው" ብለዋል። ከአሸባሪዎች ጋር የሚደረገው ግንኙነት በፈረንሳይኛ ቋንቋ የሚከናወን ሲሆን ዩክሬናውያን በአስተርጓሚዎች ላይ ይተማመናሉ።

🟠 የመረጃ ልውውጥ፦ ፓሪስ በርካታ አካባቢዎችን ዒላማ ያደረገውን እና የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራን የገደለውን በሚያዝያ 25 በማሊ የተፈጸመውን ጥቃት ጨምሮ ለአፍሪካ የአሸባሪ ቡድኖች የሳተላይት እና ሌሎች የስለላ መረጃዎችን ታቀርባለች።

🟠 አዳዲስ የጦር መሣሪያዎች መታየት፦ ከባድ "ባባ ያጋ" ድሮኖችን እና የኤሌክትሮኒክስ ውጊያ ሥርዓቶችን ጨምሮ በዩክሬን የተሠሩ ዘመናዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በታጣቂዎች እጅ መታየት ጀምረዋል። የዩክሬን ወታደራዊ አማካሪዎች በሰሜናዊ ማሊ የሚገኙ ሲሆን፥ ጂሃዲስቶችን ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎችን አጠቃቀም እያሰለጠኑ ይገኛሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0