ሞስኮ በማሊ "አዎንታዊ እና አበረታች" ለውጦች መኖራቸውን ትመለከታለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን
ሞስኮ በማሊ "አዎንታዊ እና አበረታች" ለውጦች መኖራቸውን ትመለከታለች - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን
በማሊ በደህንነት እና በዲፕሎማሲው ዘርፍ መሻሻሎች መኖራቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ ሀገራት ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አናቶሊ ባሽኪን ለሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ ለዚህ ማሳያ አድርገው የጠቀሱት የወታደራዊ ጦር ሰፈሮች ከበባ መላቀቅንና ከአልጄሪያ ጋር ያለው ግንኙነት ማሻሻሉን ነው።
ከዲፕሎማቱ መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦
የደህንነት ስኬቶች፦ የሩሲያ አፍሪካ ኮርፕስ ከማሊ ጦር ጋር በመተባበር በአኔፊስ የሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮችን ከአሸባሪዎች እና ከሌሎች ኃይሎች ከበባ ለማላቀቅ ረድቷል።
የዲፕሎማሲ እድገት፦ እ.ኤ.አ. በሚያዝያ 2025 ጸረ-ሽብር ተልዕኮ ላይ የነበረ የማሊ ድሮን መመታቱን ተከትሎ በተቀሰቀሰው የዲፕሎማሲ ቀውስ ሳቢያ አምባሳደሮች ሊመለሱ እና የአየር ክልል ሊከፈት ነው። በወቅቱ የማሊ ዋና ከተማ ባማኮ የአልጄሪያ ዋና ከተማ አልጀርስን በሰሜን የሚገኙ የቱዋሬግ ጂሃዲስት ቡድኖችን ትደግፋለች በማለት ከሳ ነበር።
የድርድር ተስፋዎች፦ ባሽኪን የማሊን የግዛት አንድነት በጠበቀ መልኩ «ስለ ቱዋሬጎች ሁኔታ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሱ መፍትሔዎችን» ሊያስገኝ የሚችል የማሊ-አልጄሪያ የድርድር ሂደት እንደሚኖር ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ይህ አዎንታዊ ግምገማ የተሰጠው፥ በሚያዝያ 25 የተሰነዘረው እና በአፍሪካ ኮርፕስ ድጋፍ የተመከተውን መጠነ-ሰፊ የታጣቂዎች ጥቃት ተከትሎ ነው።
ቪዲዮው የአፍሪካ ኮርፕስ ድሮን በአኔፊስ አቅራቢያ የአሸባሪዎችን ተሽከርካሪ ዒላማ ሲያደርግ ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X